Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ተቈጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “አንተም ብትሆን አትገባባትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 በእናንተው ምክንያት ጌታ በእኔም ላይ ደግሞ ተቆጥቶ እንዲህም አለኝ፤ ‘አንተም ደግሞ ወደዚያ አትገባም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 በእናንተው ምክንያት እግዚአብሔር በእኔም ላይ እንኳ ተቈጥቶ እንዲህ አለኝ፤ ‘ሙሴ፥ አንተም ራስህ እንኳ ወደዚያች ምድር አትገባም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት በእኔ ተቆጣ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም፤

参见章节 复制




ዘዳግም 1:37
12 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤


ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።


ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።


አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል።


ምድ​ሪ​ቱን ፊት ለፊት ታያ​ለህ እንጂ ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​ገ​ባም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።


እኔ ግን በዚ​ህች ምድር እሞ​ታ​ለሁ። ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም አል​ሻ​ገ​ርም፤ እና​ንተ ግን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ያች​ንም መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告