91 ንጉሡ ናቡከደነፆርም ሲያመሰግኑ ሰምቶ ተደነቀ፤ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም፥ “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?” ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፥ “ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው” አሉት።