24 ከዚህም በኋላ ዳንኤል ንጉሡ የባቢሎንን ጠቢባን ያጠፋ ዘንድ ወደ አዘዘው ወደ አርዮክ ገባ፤ “የባቢሎንን ጠቢባን አታጥፋቸው፤ ወደ ንጉሡ አስገባኝ፥ እኔም ሕልሙንና ፍቺውን ለንጉሡ እነግረዋለሁ” አለው