Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ቈላስይስ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ታገ​ሡ​አ​ቸው፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን የነ​ቀ​ፋ​ች​ሁ​በ​ትን ሥራ ተዉ፤ ክር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ማንም ሰው በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ ይቅር በሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤

参见章节 复制




ቈላስይስ 3:13
25 交叉引用  

ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።


እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


አሁ​ንም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ተቀ​በሉ፤ ክር​ስ​ቶስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና።


ይቅር የም​ት​ሉት ቢኖር፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ይቅር እለ​ዋ​ለሁ፤ እኔም ይቅር ያል​ሁ​ትን በክ​ር​ስ​ቶስ ፊት ስለ እና​ንተ ይቅር ብያ​ለሁ።


በን​ጽ​ሕ​ናና በዕ​ው​ቀት፥ በም​ክ​ርና በመ​ታ​ገሥ፥ በቸ​ር​ነ​ትና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ አድ​ልዎ በሌ​ለ​በት ፍቅር፥


ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ።


በፍ​ጹም የዋ​ህ​ነት ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ር​ጋ​ችሁ እየ​ታ​ገ​ሣ​ችሁ፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም እሺ እያ​ላ​ችሁ፥ በፍ​ቅር እየ​ተ​ጋ​ች​ሁና እየ​ተ​ባ​በ​ራ​ችሁ፥


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።


跟着我们:

广告


广告