Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8-9 “ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥

参见章节 复制




አሞጽ 5:8
23 交叉引用  

ጥልቅ ነገ​ርን ከጨ​ለማ ይገ​ል​ጣል፤ የሞ​ት​ንም ጥላ ወደ ብር​ሃን ያወ​ጣል።


ይኸ​ውም፥ ለተ​ግ​ሣጽ ወይም ለም​ድሩ ወይም በም​ሕ​ረት ለሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲ​ሆን ነው።


ደመ​ና​ውን በቃ​ልህ ትጠ​ራ​ዋ​ለ​ህን? ብዙ ውኃስ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ይመ​ል​ስ​ል​ሃ​ልን?


ድብ የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከ​ብና ኦሪ​ዮን የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከብ፥ የአ​ጥ​ቢያ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም፥ በአ​ዜ​ብም በኩል ያሉ​ትን የከ​ዋ​ክ​ብት ማደ​ሪ​ያ​ዎች ፈጥ​ሮ​አል።


ንጉሥ ላከ፥ ፈታ​ውም፥ የሕ​ዝ​ብም አለቃ አድ​ርጎ ሾመው።


በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤


ዕው​ሮ​ች​ንም በማ​ያ​ው​ቋት መን​ገድ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ያ​ው​ቋ​ት​ንም ጎዳና እን​ዲ​ረ​ግጡ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ጠማ​ማ​ው​ንም አቀ​ና​ለሁ። ይህ​ንም አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምም።


እንደ ዕው​ሮች ወደ ቅጥሩ ተር​መ​ሰ​መሱ፤ ዐይ​ንም እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ተር​መ​ሰ​መሱ፤ በቀ​ት​ርም ጊዜ በመ​ን​ፈቀ ሌሊት እን​ዳለ ሰው ተሰ​ና​ከሉ፤ እንደ ሙታ​ንም ይጨ​ነ​ቃሉ።


“ስለ​ዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እጄ​ንና ኀይ​ሌ​ንም አሳ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”


“ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ፥ ምድ​ርን የፈ​ጠ​ራት፥ የሠ​ራ​ትና ያጸ​ናት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”


በዚ​ያም ቀን ፀሐይ በቀ​ትር ይገ​ባል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ብር​ሃ​ንም በም​ድር ላይ በቀን ይጨ​ል​ማል።


አዳ​ራ​ሹን በሰ​ማይ የሠራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም በም​ድር ላይ የመ​ሠ​ረተ፥ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው።”


በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”


跟着我们:

广告


广告