Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ደ​ዚህ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ! እን​ደ​ዚህ ስለ​ማ​ደ​ር​ግ​ብህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም ለመ​ጥ​ራት ተዘ​ጋጅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ስለዚህ እስራኤል ሆይ፤ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤ እንደዚህም ስለማደርግብህ፣ እስራኤል ሆይ፤ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “ስለዚህ፥ እስራኤል ሆይ! እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤ እስራኤልም ሆይ! እንደዚህ ስለማደርግብህ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔም እንደዚሁ አደርግባችኋለሁ፤ ስለዚህ ይህን ስለማደርግባችሁ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር በፍርድ ለመገናኘት ተዘጋጁ!”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህ፥ እስራኤል ሆይ፥ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፥ እስራኤልም ሆይ፥ እንደዚህ ስለማደርግብህ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።

参见章节 复制




አሞጽ 4:12
20 交叉引用  

እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ደን​ግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አው​ልቁ፤ ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁኑ፤ ወገ​ባ​ች​ሁ​ንም በማቅ ታጠቁ።


ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።


አደሮ ማር በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ እን​ዲሁ ጠላ​ቶ​ች​ህን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ስም​ህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይታ​ወ​ቃል፤ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።


ወደ ተሰ​በ​ረው ቅጥር አል​ወ​ጣ​ች​ሁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን በሰ​ልፍ ትቆሙ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቅጥ​ርን አል​ሠ​ራ​ች​ሁም።


ቅጥ​ርን የሚ​ጠ​ግ​ንን፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት በፈ​ረ​ሰ​በት በኩል በፊቴ የሚ​ቆ​ም​ላ​ትን ሰው ከእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ፈለ​ግሁ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘ​ሁም።


በአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም መን​ገድ አጠ​ገብ እንደ ተራበ ድብ እገ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሥር እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም የዱር አን​በ​ሶች ይበ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት ይነ​ጣ​ጠ​ቋ​ቸ​ዋል።


የሚ​ሮጥ ሰው ማም​ለጥ አይ​ች​ልም፤ ኀይ​ለ​ኛ​ውም በብ​ር​ታቱ አይ​ዝም፤ አር​በ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም።


ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።


አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፤ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤


እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።


跟着我们:

广告


广告