Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ካህ​ናት ሆይ! ስሙ፤ በያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ላይ መስ​ክሩ፥ ይላል ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል የሰራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ስሙ፥ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥” ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ይህን ስሙ፤ በያዕቆብ ዘሮች ላይ መስክሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስሙ፥ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




አሞጽ 3:13
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁት፥ በባ​ሪ​ያ​ዎቼ በነ​ቢ​ያት የላ​ክ​ሁ​ላ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ሕጌ​ንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነ​ቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ መሰ​ከረ።


የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ል​ሱ​አ​ቸው ዘንድ ነቢ​ያ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ላ​ቸው ነበር፤ መሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ደ​መ​ጡም።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ወዮ​ላ​ቸው! በጠ​ላ​ቶች ላይ ቍጣዬ አይ​በ​ር​ድም፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ ኀጢ​አቱ በም​በ​ቀ​ል​በት ቀን የቤ​ቴ​ልን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ደግሞ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ይሰ​በ​ራሉ፤ ወደ ምድ​ርም ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ ከደ​ማ​ስቆ ወደ​ዚያ አስ​ማ​ር​ካ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የተ​ባለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤


እን​ግ​ዲህ በል​ባ​ቸው ከንቱ አሳብ እን​ደ​ሚ​ኖሩ እንደ አሕ​ዛብ እን​ዳ​ት​ኖሩ ይህን እላ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤


跟着我们:

广告


广告