Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እረኛ ከአ​ን​በሳ አፍ ሁለት እግ​ርን ወይም የጆ​ሮን ጫፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ድን፥ እን​ዲሁ በሰ​ማ​ርያ በአ​ሕ​ዛብ ፊትና በደ​ማ​ስቆ የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይድ​ናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣ እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣ በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣ እስራኤላውያን ይድናሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ከድንክ አልጋና ከአልጋ የእግር ቁራጭ ጋር ይድናሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰማርያ የሚኖሩ እስራኤላውያን ከአልጋና ከድንክ አልጋ ቊራጭ ጋር ያመልጣሉ፤ ይኸውም እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ ሁለት እግርና የጆሮ ቊራጭ ለማስጣል እንደሚችለው ዐይነት ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ በአልጋ ማዕዘን፥ በደማስቆም በምንጣፍ ላይ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ።

参见章节 复制




አሞጽ 3:12
16 交叉引用  

ሚክ​ያ​ስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልት​ሸ​ሸግ ወደ ውስ​ጠ​ኛው እል​ፍ​ኝህ በሄ​ድህ ጊዜ ታያ​ለህ” አለ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።


በጽ​ዮን ተራ​ሮች እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ አር​ሞ​ን​ዔ​ምም ጠል ነው፤ በዚያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን ሕይ​ወ​ት​ንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዝ​ዞ​አ​ልና።


በዚ​ያም ቀን ሰው በፈ​ጣ​ሪው ይታ​መ​ናል፤ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ያያሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛ​ልና፥ “አን​በሳ ወይም የአ​ን​በሳ ደቦል በን​ጥ​ቂ​ያው ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ገሣ፥ ድም​ፁም ተራ​ሮ​ችን እስ​ኪ​ሞላ በእ​ርሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ጮህ፥ እረ​ኞ​ችም ሁሉ ሲጮ​ሁ​በት ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ከድ​ም​ፃ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ነ​ግጥ፥ እነ​ር​ሱም ከቍ​ጣው ብዛት የተ​ነሣ ድል እን​ደ​ሚ​ሆ​ኑና እን​ደ​ሚ​ደ​ነ​ግጡ፥ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኮ​ረ​ብ​ታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወ​ር​ዳል።


ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”


ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥


እነሆ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች በኀ​ጢ​አ​ተኛ መን​ግ​ሥት ላይ ናቸው፤ ከም​ድ​ርም ፊት አጠ​ፋ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


跟着我们:

广告


广告