Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 9:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በር​ና​ባ​ስም አግ​ኝቶ ወደ ሐዋ​ር​ያት ወሰ​ደው፤ ጌታ​ች​ንም በመ​ን​ገድ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው፥ በደ​ማ​ስ​ቆም በኢ​የ​ሱስ ስም እንደ አስ​ተ​ማረ ነገ​ራ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ይሁን እንጂ በርናባስ ወስዶ ወደ ሐዋርያት አመጣው፤ ሳውልም በጕዞው ላይ ሳለ ጌታን እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንዴት እንደ ተናገረው እንዲሁም በደማስቆ በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንደ ሰበከ ነገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በርናባስ ግን ወስዶ ወደ ሐዋርያት አገባውና ጌታን በመንገድ እንዴት እንዳየውና እንደ ተናገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እንዴት እንደ ነገረተረከላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በርናባስ ግን ሳውልን ወደ ሐዋርያት አቀረበውና በመንገድ ሳለ ጌታ እንዴት እንደ ተገለጠለትና እንዳነጋገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንዳስተማረ ነገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በርናባስ ግን ወስዶ ወደ ሐዋርያት አገባውና ጌታን በመንገድ እንዴት እንዳየውና እንደ ተናገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እንዴት እንደ ነገረ ተረከላቸው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 9:27
20 交叉引用  

ስለ እነ​ርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውም ይህ ነገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዘንድ ተሰማ፤ በር​ና​ባ​ስ​ንም ወደ አን​ጾ​ኪያ ላኩት።


ከዚ​ህም በኋላ በር​ና​ባስ ሳው​ልን ሊፈ​ልግ ወደ ጠር​ሴስ ሄደ፤ በአ​ገ​ኘ​ውም ጊዜ ወደ አን​ጾ​ኪያ ወሰ​ደው።


በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው።


ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው።


በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ዘንድ ትር​ጓ​ሜዉ የመ​ጽ​ና​ናት ልጅ የሚ​ሆን በር​ና​ባስ የተ​ባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚ​ሉት አንድ የቆ​ጵ​ሮስ ሰው ነበር።


ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


ከግ​ሪክ ሀገር መጥ​ተው የነ​በ​ሩ​ት​ንም አይ​ሁድ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ሊገ​ድ​ሉት ፈለጉ።


ከሁ​ሉም በኋላ ጭን​ጋፍ ለም​መ​ስል ለእኔ ታየኝ።


ወይስ ሥራን ለመ​ተው መብት የሌ​ለን እኔና በር​ና​ባስ ብቻ ነን?


ከአ​ይ​ሁድ ወገ​ንም ወደ​ዚህ ግብር የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ በር​ና​ባ​ስም እንኳ በግ​ብ​ዝ​ነ​ታ​ቸው ተባ​በረ።


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


跟着我们:

广告


广告