ሐዋርያት ሥራ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 የሰሙትም ሁሉ አደነቁ፤ እንዲህም አሉ፥ “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ይጠላቸው የነበረው ይህ አይደለምን? ስለዚህ ወደዚህ የመጣው እያሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን?” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 የሰሙትም ሁሉ በመገረም፣ ይህ ሰው “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረ አይደለምን? ደግሞም ወደዚህ የመጣው እነርሱን አስሮ ወደ ካህናት አለቆች ሊወስዳቸው አልነበረምን?” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና “ይህ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋ አይደለምን? ስለዚህስ ታስረው ወደ ካህናት አለቆች ይወስዳቸው ዘንድ ወደዚህ አልመጣምን?” አሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 የሰሙትም ሁሉ፥ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ የሚያጠፋ የነበረ አይደለምን? ወደዚህስ የመጣው እነርሱን እያሰረ ወደ ካህናት አለቆች ለመውሰድ አይደለምን?” በማለት ይደነቁ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና፦ “ይህ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋ አይደለምን? ስለዚህስ ታስረው ወደ ካህናት አለቆች ይወስዳቸው ዘንድ ወደዚህ አልመጣምን?” አሉ። 参见章节 |