Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 8:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ከዚያ በኋላ ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ፤ ቂሳርያም እስኪደርስ ድረስ በሚያልፍባቸው ከተሞች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ፤ ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ፊልጶስ ግን በአዞጦስ ተገኘ፤ ወደ ቂሳርያም እስከ መጣ ድረስ በየከተሞቹ ሁሉ እየሄደ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ፥ ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 8:40
21 交叉引用  

የተደባለቀ ወገን በአዛጦን ይቀመጣል፥ የፍልስጥኤማውያንንም ትዕቢት አጠፋለሁ።


በቂ​ሳ​ር​ያም ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢጣ​ሊቄ ለሚ​ሉት ጭፍ​ራም የመቶ አለቃ ነበር።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ቂሳ​ርያ ከተማ ገባ፤ ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም ዘመ​ዶ​ቹ​ንና የቅ​ርብ ወዳ​ጆ​ቹን ጠርቶ ይጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር።


በዚ​ያ​ችም ሰዓት ከቂ​ሳ​ርያ ወደ እኔ የተ​ላኩ ሦስት ሰዎች መጡ፤ እኔ ባለ​ሁ​በት ግቢ በርም ቆሙ።


ሄሮ​ድስ ግን አስ​ፈ​ልጎ ባጣው ጊዜ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን መረ​መረ፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ አዘዘ፤ ከዚ​ህም በኋላ ከይ​ሁዳ ወደ ቂሳ​ርያ ወርዶ በዚያ ተቀ​መጠ።


ወደ ቂሳ​ር​ያም ደረሰ፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ ከሰጠ በኋላ ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደ።


ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከቂ​ሳ​ርያ አብ​ረ​ውን የመጡ ነበሩ፤ ሄደ​ንም ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን ከሆ​ነው በቆ​ጵ​ሮስ በሚ​ኖ​ረው በም​ና​ሶን ቤት አደ​ርን።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።


ከመቶ አለ​ቆ​ችም ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “ከወ​ታ​ደ​ሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁለት መቶ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ምረጡ፤ ከሌ​ሊ​ቱም በሦ​ስት ሰዓት ወደ ቂሣ​ርያ ይሂዱ” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢ​ውም ደረሱ፤ የተ​ላ​ከ​ው​ንም ደብ​ዳቤ ለአ​ገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም ወደ እርሱ አቀ​ረ​ቡት።


ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።


ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን በቂ​ሣ​ርያ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ እር​ሱም ራሱ ወደ​ዚ​ያው በቶሎ እን​ደ​ሚ​ሄድ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


ስም​ንት ወይም ዐሥር ቀን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ነ​በተ በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጦ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።


እነ​ር​ሱም ከመ​ሰ​ከ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ በብ​ዙ​ዎች የሰ​ማ​ርያ መን​ደ​ሮ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ።


ወን​ድ​ሞ​ችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳ​ርያ አወ​ረ​ዱት፤ ከዚ​ያም ወደ ጠር​ሴስ ላኩት።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ።


跟着我们:

广告


广告