Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ጥዋት ገስ​ግ​ሠው ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገቡና አስ​ተ​ማሩ፤ ሊቀ ካህ​ና​ቱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ግን ጉባ​ኤ​ው​ንና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ሁሉ ሰበ​ሰቡ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ወኅኒ ቤት ላኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንደ ነጋም፣ በተነገራቸው መሠረት ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ገብተው ሕዝቡን ማስተማር ጀመሩ። ሊቀ ካህናቱና ከርሱ ጋራ የነበሩት መጥተው የአይሁድን ሸንጎና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጉባኤ በሙሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፤ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሐዋርያቱም ትእዛዙን ተቀብለው በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና ማስተማር ጀመሩ። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው የሸንጎውን አባሎችና የአይሁድ ሽማግሌዎችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡአቸው ሰዎችን ወደ ወህኒ ቤት ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፥ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 5:21
16 交叉引用  

ድን​ቅ​ንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገ​ር​ንም በኤ​ር​ትራ ባሕር ያደ​ረ​ገ​ውን።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


በነ​ጋም ጊዜ፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ወሰ​ዱት።


ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


በሕ​ዝ​ብም ሁሉ ዘንድ ባየ​ኸ​ውና በሰ​ማ​ኸው ምስ​ክር ትሆ​ነ​ዋ​ለህ።


እን​ዲ​ቀ​ጡም ከዚያ ያሉ​ትን አስሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ወደ አሉ ወን​ድ​ሞች እን​ድ​ሄድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ የተ​ቀ​በ​ል​ኋ​ቸው ሊቀ ካህ​ና​ቱና መም​ህ​ራን ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ራሉ።


ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።


አም​ጥ​ተ​ውም በሸ​ንጎ መካ​ከል አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ሊቀ ካህ​ና​ቱም መረ​መ​ራ​ቸው፤


በሸ​ን​ጎ​ዉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የከ​በረ የኦ​ሪት መም​ህር ስሙን ገማ​ል​ያል የሚ​ሉት አንድ ፈሪ​ሳዊ ተነሣ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ከጉ​ባ​ኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው አዘዘ።


እነ​ር​ሱም ከሸ​ን​ጎው ፊት ደስ እያ​ላ​ቸው ወጡ፤ ስለ ስሙ መከራ ይቀ​በሉ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ አድ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


跟着我们:

广告


广告