Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ሂዱ፤ በቤተ መቅደሱም አደባባይ ቁሙ፤ የዚህንም ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ ንገሩ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ፤” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ሂዱ! በቤተ መቅደስ ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ንገሩ!” አላቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 “ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ” አላቸው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 5:20
21 交叉引用  

ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።


ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


ትእ​ዛ​ዙም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም የም​ና​ገ​ረ​ውን አብ እን​ዳ​ለኝ እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ።”


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን?


አን​ተና ቤተ ሰቦ​ችህ ሁሉ የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ነገር እርሱ ይነ​ግ​ር​ሃል’ እንደ አለው ነገ​ረን።


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


跟着我们:

广告


广告