28 እጅህና ምክርህ እንዲደረግ የወሰኑትን ይፈጽሙ ዘንድ።
28 ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።
28 እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኀይል አለ፤ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።
እነሆ፥ ዛሬ ጀመርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እንደሚያፈራርቅ።
ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል።
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክርን ከሚመክር በግብሩም ገናና ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል። እናንተ ግን ከንቱ መጽናናትን ታበዙ ዘንድ ትሻላችሁ።
“እኔ ጥንት የሠራሁትን አልሰማህምን? እኔ በቀድሞ ዘመን እንዳደረግሁት፥ አሁንም አሕዛብን በምሽጎቻቸው፥ በጽኑ ከተሞቻቸው የሚኖሩትንም ያጠፉ ዘንድ አዘዝሁ።
የእግዚአብሔርን ሕሊና ያወቀ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያማከረው ማን ነው?
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
“እናይ ዘንድ፥ ሥራውን ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮላቸው!
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።
እንዲህ ከሆነስ ‘እንደዚህ ሊሆን ይገባል፤’ የሚሉ መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?”
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በእጁ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት።”
እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት።
እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በነቢያት ሁሉ አፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረ እንዲሁ ፈጸመ።
እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰን በእርሱ ርስትን ተቀበልን።
ስለዚህም እግዚአብሔር ተስፋውን ለሚወርሱ ሰዎች ምክሩን እንደማይለውጥ ሊገልጥ ወደደ፤ እንደማይለውጥም በመሓላ አጸናው።