ሐዋርያት ሥራ 4:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አንተ ራስህ በአባታችን በባሪያህ በዳዊት አፍ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለህ የተናገርህ፦ አሕዛብ ለምን ተሰበሰቡ? ሕዝቡስ ለምን ከንቱ ነገርን ተናገሩ? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በመንፈስ ቅዱስም አማካይነት በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “ ‘አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ ‘አሕዛብ ለምን አጉረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ የተናገርክ አንተ ነህ፤ ‘አሕዛብ ስለምን ተቈጡ? ሕዝቦችስ ስለምን በከንቱ ዶለቱ? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ፦ አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? 参见章节 |