Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋራ እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት መናገራቸውን የሸንጎ አባሎች ባዩ ጊዜ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ያውቁ ስለ ነበረ ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ዐወቁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 4:13
22 交叉引用  

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች።


ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን “አነጋገርህ ይገልጥሃልና፥ በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን፥ “ሂዱና የም​ን​በ​ላ​ውን የፋ​ሲካ በግ አዘ​ጋ​ጁ​ልን” አላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት።


አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ሳይ​ማር መጽ​ሐ​ፍን እን​ዴት ያው​ቃል?” እያሉ ትም​ህ​ር​ቱን አደ​ነቁ።


ኦሪ​ትን ከማ​ያ​ውቁ ከእ​ነ​ዚህ ስሑ​ታን ሕዝብ በቀር፤ እነ​ር​ሱም የተ​ረ​ገሙ ናቸው።”


ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው።


ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ።


በር​ና​ባ​ስም አግ​ኝቶ ወደ ሐዋ​ር​ያት ወሰ​ደው፤ ጌታ​ች​ንም በመ​ን​ገድ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው፥ በደ​ማ​ስ​ቆም በኢ​የ​ሱስ ስም እንደ አስ​ተ​ማረ ነገ​ራ​ቸው።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አብ​ሮ​አ​ቸው ይገ​ባና ይወጣ ነበረ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ስምም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምር ነበር።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​በ​ኞ​ችን ሊያ​ሳ​ፍር የዚ​ህን ዓለም ሰነ​ፎች መረጠ፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ደካ​ሞች መረጠ።


በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።


እን​ግ​ዲህ ይህን ያህል ተስፋ ካለን በግ​ልጥ ፊት ለፊት ልን​ቀ​ርብ እን​ች​ላ​ለን።


跟着我们:

广告


广告