Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ በቅ​ዱ​ሳን ነቢ​ያቱ አፍ እስከ ተና​ገ​ረው የመ​ደ​ራ​ጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀ​በ​ለው ዘንድ ይገ​ባል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፣ ሁሉን ነገር እስከሚያድስበት ዘመን ድረስ እርሱ በሰማይ ይቈይ ዘንድ ይገባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እርሱም በሰማይ የሚቈየው እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው ዓለም ሁሉ እስኪታደስ ድረስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 3:21
16 交叉引用  

ፈራ​ጆ​ች​ሽ​ንም እንደ ቀድሞ፥ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ መጀ​መ​ሪያ ጊዜ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ የጽ​ድቅ ከተማ፥ የታ​መ​ነ​ችም ጽዮን ርእሰ ከተማ ተብ​ለሽ ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።


ከጥ​ንት ጀምሮ በነ​በሩ በቅ​ዱ​ሳን በነ​ቢ​ያት አፍ እንደ ተና​ገረ።


እነ​ር​ሱም፥ “እና​ንተ የገ​ሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየ​አ​ያ​ችሁ ለምን ቆማ​ች​ኋል? ይህ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ያረ​ገው ኢየ​ሱስ፥ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ሲያ​ርግ እን​ዳ​ያ​ች​ሁት እን​ዲሁ ዳግ​መኛ ይመ​ጣል” አሏ​ቸው።


ለሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትም ሁሉ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በስሙ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ነቢ​ያት ሁሉ ምስ​ክ​ሮቹ ናቸው።”


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ይሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመ​ለ​ሱም።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም የይ​ቅ​ርታ ዘመን ይመ​ጣል። አስ​ቀ​ድሞ የመ​ረ​ጠ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።


ነገር ግን አስቶ በባ​ር​ነት ከሚ​ገ​ዛው ከዚህ ወጥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ አገ​ኙ​አት የነ​ጻ​ነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው።


ከጥ​ንት ጀምሮ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ዐይ​ነ​ትና በብዙ ጎዳና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በነ​ቢ​ያት ተና​ገረ።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


እርሱም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


跟着我们:

广告


广告