Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አለ​ቆ​ቻ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረጉ ይህን ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አው​ቃ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ እናንተ ይህን ያደረጋችሁት እንደ አለቆቻችሁ ሁሉ ባለማወቅ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “አሁንም ወንድሞቼ ሆይ! በኢየሱስ ላይ ያደረጋችኹትን ነገር እናንተም እንዳለቆቻችሁ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 3:17
23 交叉引用  

አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህን ነገር ማን እን​ዳ​ደ​ረ​ገው አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ አን​ተም ደግሞ ምንም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም፤ እኔም ከዛሬ በቀር አል​ሰ​ማ​ሁም።”


እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤


ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


እነ​ሆም፥ የም​ድ​ሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ች​ንም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ አሁ​ንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበ​ል​ጣ​ልና ልወ​ጋ​ቸ​ውና ከም​ድ​ሪቱ ላሳ​ድ​ዳ​ቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገ​ም​ልኝ፤ አንተ የመ​ረ​ቅ​ኸው ምሩቅ፥ የረ​ገ​ም​ኸ​ውም ርጉም እንደ ሆነ አው​ቃ​ለ​ሁና” ብሎ ይጠ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


ጲላ​ጦ​ስም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ች​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ጠራ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና።


ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ችሁ አብ​ንም፥ እኔ​ንም ስላ​ላ​ወቁ ነው።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ግን እር​ሱን አላ​ወ​ቁም፤ የነ​ቢ​ያት መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ ሲያ​ነቡ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ ነገር ግን ይሙት በቃ ፈረ​ዱ​በት፥ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ፈጸ​ሙ​በት።


እን​ዲ​ቀ​ጡም ከዚያ ያሉ​ትን አስሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ወደ አሉ ወን​ድ​ሞች እን​ድ​ሄድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ የተ​ቀ​በ​ል​ኋ​ቸው ሊቀ ካህ​ና​ቱና መም​ህ​ራን ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ራሉ።


“እኔም ብዙ ጊዜ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ስም ላይ ክፉ ነገር ላደ​ርግ ቈርጬ ነበር።


የአ​ይ​ሁድ ታላ​ላቅ ሰዎ​ችም እን​ዲህ አሉት፥ “ለእ​ኛስ ከይ​ሁዳ ሀገር ስለ አንተ መል​እ​ክት አል​ደ​ረ​ሰ​ንም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከመ​ጡት ወን​ድ​ሞ​ችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወ​ራን፥ የነ​ገ​ረ​ንም የለም።


አሮ​ን​ንም፦ ‘በፊት በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክ​ትን ሥራ​ልን፤ ያ ከም​ድረ ግብፅ ያወ​ጣን ሙሴ የሆ​ነ​ውን አና​ው​ቅ​ምና’ አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን?


የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።


ልቡ​ና​ቸው የተ​ጨ​ፈነ ነው፤ በስ​ን​ፍ​ና​ቸ​ውና በድ​ን​ቍ​ር​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሕይ​ወት የተ​ለዩ ናቸው።


ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


跟着我们:

广告


广告