Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 28:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በዚ​ያም ያሉት ወን​ድ​ሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍ​ዩስ ፋሩስ እስ​ከ​ሚ​ባ​ለው ገበ​ያና እስከ ሦስ​ተ​ኛው ማረ​ፊያ ድረስ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉን፤ ጳው​ሎ​ስም ባያ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ልቡም ተጽ​ናና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በዚያ የነበሩ ወንድሞችም መምጣታችንን ስለ ሰሙ፣ እስከ አፍዩስ ፋሩስ እንዲሁም “ሦስት ማደሪያ” እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን ወጡ፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ሊቀበሉን ወጡ፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በሮም ያሉ ምእመናን ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዮስ ገበያና “ሦስት ማደሪያዎች” እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ፤ ጳውሎስ እነርሱን ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነና ተጽናና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ሊቀበሉን ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 28:15
22 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል።


የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት።


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


እር​ሱም ተቀ​ብሎ አሳ​ደ​ራ​ቸው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በኢ​ዮጴ ከተማ ከሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችም አብ​ረ​ውት የሄዱ ነበሩ።


ጴጥ​ሮ​ስም በገባ ጊዜ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ተቀ​በ​ለው፤ ከእ​ግሩ በታ​ችም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


ሐዋ​ር​ያ​ትና በይ​ሁዳ የነ​በሩ ወን​ድ​ሞ​ችም አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ ተቀ​በሉ ሰሙ።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም፦ ‘ሳት​ጠ​ራ​ጠር አብ​ረ​ሃ​ቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ተከ​ት​ለ​ውኝ መጡና ወደ​ዚያ ሰው ቤት ገባን።


እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን።


በዚ​ያም ወን​ድ​ሞ​ችን አግ​ኝ​ተን ተቀ​በ​ሉን፤ በእ​ነ​ርሱ ዘን​ድም ሰባት ቀን እን​ድ​ን​ቀ​መጥ ለመ​ኑን፤ ከዚ​ያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረ​ስን።


ወደ አስ​ባ​ንያ ስሄድ እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋ​ላም ከእ​ና​ንተ ወደ​ዚያ እሄ​ዳ​ለሁ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘወ​ትር ድል በመ​ን​ሣቱ የሚ​ጠ​ብ​ቀን፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ የዕ​ው​ቀ​ቱን መዓዛ በእኛ የሚ​ገ​ልጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


መከራ እቀ​በል በነ​በ​ረ​በት ጊዜ አል​ሰ​ለ​ቻ​ች​ሁ​ኝም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ፥ እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ተቀ​በ​ላ​ች​ሁኝ እንጂ በሰ​ው​ነቴ አል​ና​ቃ​ች​ሁ​ኝም።


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤


ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።


跟着我们:

广告


广告