ሐዋርያት ሥራ 27:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 መልሕቁንም ፈትተው በባሕር ላይ ጣሉት፤ የሚያቆሙበትንም አመቻችተው እንደ ነፋሱ አነፋፈስ መጠን ትንሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳርቻም ሄድን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፤ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 መልሕቆቹን ፈተው በባሕር ውስጥ ለቀቁአቸው፤ በዚያኑ ጊዜም የመቅዘፊያውን ገመዶች ፈቱ፤ ከዚህ በኩል ያለውን ሸራ ወደ ነፋሱ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፥ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። 参见章节 |