ሐዋርያት ሥራ 25:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በማግሥቱም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመሳፍንቱና ከከተማው ታላላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በማግስቱም አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር መጥተው፣ ከከፍተኛ መኰንኖችና ከከተማዪቱ ታላላቅ ሰዎች ጋራ ወደ መሰብሰቢያው አዳራሽ ገቡ፤ በፊስጦስም ትእዛዝ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰውና በታላቅ ግርማ ሆነው በጦር አለቆችና በከተማው ታላላቅ ሰዎችም ታጅበው መጡና ወደ ፍርድ አዳራሽ ገቡ፤ ከዚያም በኋላ ፊስጦስ ጳውሎስን አስጠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት። 参见章节 |