ሐዋርያት ሥራ 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 የመቶ አለቃውንም ጳውሎስን እንዲጠብቀው፥ በሰፊ ቦታም እንዲያኖረው፥ እንዳያጠብበትም፥ ሊያገለግሉት በመጡ ጊዜም ከወዳጆቹ አንዱን ስንኳ እንዳይከለክልበት አዘዘ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከዚያም ለጳውሎስ መጠነኛ ነጻነት እየሰጠ እንዲጠብቀውና ወዳጆቹም ገብተው እንዲያገለግሉት ፈቃድ ይሰጣቸው ዘንድ የመቶ አለቃውን አዘዘው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 የመቶውንም አለቃ ጳውሎስን ሲጠብቅ እንዲያደላለት፥ ከወዳጆቹም ማንም ሲያገለግለው ወይም ወደ እርሱ ሲመጣ እንዳይከለክልበት አዘዘው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 የመቶውንም አለቃ ጳውሎስን ሲጠብቅ እንዲያደላለት፥ ከወዳጆቹም ማንም ሲያገለግለው ወይም ወደ እርሱ ሲመጣ እንዳይከለክልበት አዘዘው። 参见章节 |