Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የመቶ አለ​ቃ​ውም ልጁን ይዞ ወደ የሻ​ለ​ቃው ወሰ​ደ​ውና፥ “የሚ​ነ​ግ​ርህ ስለ አለው እስ​ረ​ኛው ጳው​ሎስ ይህን ልጅ ወደ አንተ እን​ዳ​ደ​ር​ሰው ለመ​ነኝ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሱም ወደ ጦር አዛዡ ወሰደው። የመቶ አለቃውም፣ “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ፣ ይህ ጕልማሳ የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና “ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ፤” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የመቶ አለቃውም ልጁን ወደ አዛዡ ይዞ ገባና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ልጅ ለአንተ የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና፦ ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ አለው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 23:18
11 交叉引用  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።


ጭፍ​ሮ​ችና የሺ አለ​ቃው፥ የአ​ይ​ሁ​ድም ሎሌ​ዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘው አሰ​ሩት።


በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር።


ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው።


የሻ​ለ​ቃ​ውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብ​ቻው ገለል አድ​ርጎ፥ “የም​ት​ነ​ግ​ረኝ ነገሩ ምን​ድ​ነው?” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።


ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ።


ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ሆይ ስለ እና​ንተ እኔ ጳው​ሎስ የክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረ​ኛው ነኝ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለተ​ጠ​ራ​ሁ​ላት አጠ​ራር በሚ​ገባ ትኖሩ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረኛ የሆ​ንሁ እኔ ጳው​ሎስ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ይልቁንም እንደዚህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው፥ አሁንም ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ፥ ስለ ፍቅር እለምናለሁ።


跟着我们:

广告


广告