Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ያን​ጊ​ዜም ጳው​ሎስ ሰዎ​ችን ይዞ በማ​ግ​ሥቱ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነጻ። የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ው​ንም ወራት መድ​ረ​ሱን ከነ​ገ​ራ​ቸው በኋላ ሁሉም እየ​አ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ይዞ​አ​ቸው ገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ጳውሎስም በማግስቱም ሰዎቹን ይዞ ሄደ፤ ዐብሯቸውም የመንጻቱን ሥርዐት ፈጸመ። ከዚያም የመንጻቱ ሥርዐት መቼ እንደሚያበቃና የእያንዳንዳቸውም መሥዋዕት መቼ እንደሚቀርብ ለማስታወቅ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር እየነጻ፥ መንጻታቸውን የሚፈጽሙበትን ቀን አስታውቆ ወደ መቅደስ ገባ። በዚያም ቀን ስለ እያንዳንዳቸው መሥዋዕትን አቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ሰዎቹን ወሰደና በማግስቱ ከእነርሱ ጋር ራሱን አነጻ፤ የሚነጹባቸው ቀኖች መቼ እንደሚሆንና ስለ እያንዳንዱም የሚሰጠው የመባ ገንዘብ የሚከፈልበት ጊዜ መቼ እንደሚሆን ለማስታወቅ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር እየነጻ፥ መንጻታቸውን የሚፈጽሙበትን ቀን አስታውቆ ወደ መቅደስ ገባ። በዚያም ቀን ስለ እያንዳንዳቸው መሥዋዕትን አቀረቡ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 21:26
6 交叉引用  

“የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር።


ይዘ​ሃ​ቸው ሂድ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ራስ​ህን አንጻ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ላጩ ስለ እነ​ርሱ ገን​ዘብ ክፈ​ል​ላ​ቸው፤ የሚ​ያ​ሙ​ህም በሐ​ሰት እንደ ሆነ፥ አን​ተም የኦ​ሪ​ትን ሕግ እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ ሁሉም ያው​ቃሉ።


በዚ​ያም ጊዜ ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ከሕ​ዝብ ጋር በመ​ከ​ራ​ከር፥ ወይም በፍ​ጅት ሳይ​ሆን በመ​ቅ​ደስ ስነጻ አገ​ኙኝ።


አይ​ሁ​ድን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ እንደ አይ​ሁ​ዳዊ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ከኦ​ሪት በታች ያሉ​ትን እጠ​ቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦ​ሪት በታች ሳል​ሆን ከኦ​ሪት በታች ላሉት ከኦ​ሪት በታች እን​ዳለ ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告