Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 20:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሠርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 20:29
18 交叉引用  

ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?


“የማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዬን በጎች ለሚ​ያ​ጠ​ፉና ለሚ​በ​ትኑ እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፣ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትጨልማለች።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።


ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተ​ኵ​ላ​ዎች መካ​ከል እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።


“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።


ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም።


ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው።


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን በኀጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ፤” ብለዋችኋልና።


跟着我们:

广告


广告