Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚህች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ ከእናንተ አንድ እንኳ ቢጠፋ ኀላፊነት እንደሌለብኝ በዛሬው ቀን አስገነዝባችኋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 20:26
14 交叉引用  

ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአ​በ​ኔር ደም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መን​ግ​ሥ​ቴም ንጹሕ ነው፤


መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?


እኔም ዛሬ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እና​ን​ተም በላ​ከኝ ነገር ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


ከዚ​ያም አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት ሕዝብ አል​ዓ​ዛ​ርን ከመ​ቃ​ብር እንደ ጠራው፥ ከሙ​ታ​ንም እንደ አስ​ነ​ሣው መሰ​ከ​ሩ​ለት።


ያየ​ውም መሰ​ከረ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት ነው፤ እር​ሱም እና​ንተ ልታ​ምኑ እው​ነት እን​ደ​ሚ​ና​ገር ያው​ቃል።


እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም።


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ታገ​ሡን፥ የበ​ደ​ል​ነው የለም፤ የገ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ ያጠ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ የቀ​ማ​ነ​ውም የለም።


እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና።


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


跟着我们:

广告


广告