Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 20:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ዐምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና፤ ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 20:16
17 交叉引用  

የሰ​ባ​ቱ​ንም ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እር​ሱም የስ​ንዴ መከር መጀ​መ​ሪያ ነው፤ በዓ​መ​ቱም መካ​ከል የመ​ክ​ተቻ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።


ጴጥ​ሮ​ስም በሩን አን​ኳኳ፤ ሮዴ የም​ት​ባል ብላ​ቴ​ናም ልት​ከ​ፍ​ት​ለት መጣች።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤


ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ አጵ​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሳለ፥ ጳው​ሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌ​ሶን መጣ፤ በዚ​ያም ጥቂት ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገኘ።


ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።


ኀም​ሳው ቀንም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


እኛ ግን በመ​ር​ከብ ሆነን ወደ አሶስ ሄድን፤ ከዚያ ጳው​ሎ​ስን ልን​ቀ​በ​ለው እንሻ ነበ​ርና፤ እን​ደ​ዚሁ በእ​ግር እን​ደ​ሚ​መጣ ነግ​ሮን ነበ​ርና ተቀ​በ​ል​ነው።


ወደ እር​ሱም በመጡ ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወደ እስያ ከገ​ባ​ሁ​በት ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ጀምሮ በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ና​ንተ ዘንድ እንደ ተቀ​መ​ጥሁ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም እነሆ በመ​ን​ፈስ ታሥሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን በዚያ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝን አላ​ው​ቅም።


ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ።


እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን።


በዚ​ያም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገ​ኘ​ንና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን፤ እነ​ር​ሱም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጾ​ላ​ቸው ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ነገ​ሩት።


ከብዙ ዓመ​ታ​ትም በኋላ ለወ​ገ​ኖች ምጽ​ዋ​ት​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ላደ​ርግ መጣሁ።


እስከ በዓለ ኀምሳ በኤ​ፌ​ሶን እቈ​ያ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告