Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጳው​ሎ​ስም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ አፉን ሊከ​ፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋል​ዮስ መልሶ አይ​ሁ​ድን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ አይ​ሁድ ሆይ፥ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖ​ር​በት አቤ​ቱ​ታ​ች​ሁን በሰ​ማ​ሁና ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጳውሎስ ሊናገር ገና አፉን ሲከፍት፣ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፤ “የአይሁድ ሰዎች ሆይ፤ ያቀረባችሁት ጕዳይ ስለ ዐመፅ ወይም ስለ ከባድ ወንጀል ቢሆን ኖሮ ላደምጣችሁ በተገባኝ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጳውሎስም አፉን ሊከፍት ባሰበ ጊዜ፥ ጋልዮስ አይሁድን “አይሁድ ሆይ! ዐመፅ ወይም ክፉ በደል በሆነ እንድታገሣችሁ በተገባኝ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጳውሎስ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሳለ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የአይሁድ ወገኖች! በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞባችሁ ቢሆን ኖሮ ክሳችሁን በትዕግሥት በሰማሁ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጳውሎስም አፉን ሊከፍት ባሰበ ጊዜ፥ ጋልዮስ አይሁድን፦ አይሁድ ሆይ፥ ዓመፅ ወይም ክፉ በደል በሆነ እንድታገሣችሁ በተገባኝ፤

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 18:14
17 交叉引用  

አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦


እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሽን​ገ​ላ​ንና ክፋ​ትን ሁሉ የተ​መ​ላህ፥ የሰ​ይ​ጣን ልጅ፥ የጽ​ድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀ​ና​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ማጣ​መ​ም​ህን ትተው ዘንድ እንቢ አል​ህን?


አርባ ዘመ​ንም በም​ድረ በዳ መገ​ባ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ከበ​ደ​ልሁ ወይም ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃኝ የሠ​ራ​ሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይ​ፈ​ረ​ድ​ብኝ አል​ልም፤ ነገር ግን እነ​ዚህ በደል የሌ​ለ​ብ​ኝን በከ​ንቱ የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ከሆነ፥ ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጠኝ ለማን ይቻ​ለ​ዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ብያ​ለሁ።”


ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።


ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መል​ካም ለሚ​ሠራ የሚ​አ​ስ​ፈሩ አይ​ደ​ሉም፤ ሹሞ​ችን እን​ዳ​ት​ፈራ ብት​ፈ​ልግ መል​ካም አድ​ርግ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤


በስ​ን​ፍ​ናዬ እና​ገር ዘንድ ጥቂት ልት​ታ​ገ​ሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆ​ንም በር​ግጥ ታገ​ሡኝ፤


ወደ እና​ንተ የመ​ጣና እኛ ወደ አላ​ስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወደ ሌላ ኢየ​ሱስ የጠ​ራ​ችሁ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት ሌላ መን​ፈስ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሌላ ወን​ጌል ቢኖር ልት​ጠ​ብ​ቁን ይገ​ባል።


እርሱ ራሱም ደካማ ነውና ባለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ከሳቱ ሰዎች ጋር መከ​ራን ሊቀ​በል ይች​ላል።


跟着我们:

广告


广告