Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከኤፊቆሮስና ከኢስጦኢክ የፍልስፍና ወገን የሆኑትም ወደ እርሱ መጥተው ይከራከሩት ነበር። አንዳንዶቹ፣ “ይህ ለፍላፊ ምን ለማለት ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው የምሥራች ሲሰብክ ሰምተው፣ “ስለ አዳዲስ ባዕዳን አማልክት የሚናገር ይመስላል” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል?” አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው “አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል፤” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ኤፒኮሮሶችና እስቶይኮች የተባሉ ፈላስፎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይከራከሩ ነበር። አንዳንዶቹ “ይህ ለፍላፊ ምን ማለት ይፈልጋል?” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “ስለ አዳዲስ አማልክት የሚናገር ይመስላል” ይሉ ነበር፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስ የኢየሱስንና የትንሣኤውን መልካም ዜና ስላበሠረ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም፦ ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው፦ አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 17:18
16 交叉引用  

በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የነገርህን ጥበብ እንዳይንቅብህ።


ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ሲከብቡአቸው ጻፎችም ከእነርሱ ጋር ሲከራከሩ አየ።


በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነ​ግ​ራ​ቸው ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን አጽ​ን​ተው ይጣ​ሉት፥ ይቀ​የ​ሙ​ትም ጀመር።


ክር​ስ​ቶስ እን​ደ​ሚ​ሞት፥ ከሙ​ታን ተለ​ይ​ቶም አስ​ቀ​ድሞ እን​ደ​ሚ​ነሣ፥ ለሕ​ዝ​ብና ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ፥ ለመ​ላ​ውም ዓለም እን​ደ​ሚ​ያ​በራ።”


ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ።


ሁል​ጊ​ዜም በቤተ መቅ​ደ​ስና በቤት ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ማስ​ተ​ማ​ር​ንና መስ​በ​ክን አል​ተ​ዉም።


የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።


ጥበ​በ​ኞች ነን ሲሉ አላ​ዋ​ቆች ሆኑ።


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


እኛስ ስለ ክር​ስ​ቶስ ብለን አላ​ዋ​ቂ​ዎች ነን፤ እና​ንተ ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ጠቢ​ባን ናችሁ፤ እኛ ደካ​ሞች ነን፤ እና​ንተ ግን ብር​ቱ​ዎች ናችሁ፤ እና​ንተ ክቡ​ራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተ​ዋ​ረ​ድን ነን።


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


跟着我们:

广告


广告