Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትም በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸኑ፤ ዕለት ዕለ​ትም ቍጥ​ራ​ቸው ይበዛ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አብያተ ክርስቲያናትም በእምነት እየበረቱና ዕለት ዕለትም በቍጥር እየጨመሩ ይሄዱ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፤ በቍጥር ም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ አብያተ ክርስቲያን በእምነት ጠነከሩ፤ ቊጥራቸውም በየቀኑ እየጨመረ ይሄድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አብያተ ክርስቲያናትም በሃያማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 16:5
23 交叉引用  

ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁ​ሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወ​ጡም ኢዮ​ሣ​ፍጥ ቆመና፥ “ይሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፥ ትጸ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ በነ​ቢ​ዩም እመኑ፤ ነገ​ሩም ይቀ​ና​ላ​ች​ኋል” አለ።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ራስ ሳም​ሮን ነው፤ የሳ​ም​ሮ​ንም ራስ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ነው። ባታ​ምኑ አት​ጸ​ኑም።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ወደ ጌታም ተመ​ል​ሰው ያመኑ ሰዎች ቍጥ​ራ​ቸው በዛ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም።


በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅ​ያም እየ​ዞረ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን አጽ​ናና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ዘንድ መወ​ደድ ነበ​ራ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ድ​ኑ​ትን ዕለት ዕለት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይጨ​ምር ነበር።


ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ።


በጌ​ታ​ች​ንም የሚ​ያ​ምኑ ብዙ​ዎች ይጨ​መሩ ነበር፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምእ​መ​ናን እጅግ በዙ፤ ከካ​ህ​ና​ትም መካ​ከል ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ።


በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ።


ይህም በነ​ቢ​ያት ቃልና የዘ​ለ​ዓ​ለም ገዥ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በዚህ ወራት ተገ​ለጠ፤ አሕ​ዛብ ሁሉ ይህን ሰም​ተ​ውና ዐው​ቀው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያምኑ ዘንድ።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ።


እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ።


ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።


ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።


በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።


跟着我们:

广告


广告