Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 16:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እነ​ር​ሱም፥ “በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እመን፤ አን​ተና ቤተ ሰብ​ህም ሁሉ ትድ​ና​ላ​ችሁ” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ፤” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ ትድናለህ፤ ቤተሰቦችህም ይድናሉ” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እነርሱም፦ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ” አሉት።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 16:31
31 交叉引用  

ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ሩኝ ሌላ መን​ገ​ድና ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


ለተ​ቀ​በ​ሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚ​ያ​ምኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ዲ​ሆኑ ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።


የአ​ባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወል​ድን አይቶ የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ ነው፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።”


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው።


ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ እን​ድን ዘንድ እን​ታ​መ​ና​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ ይድ​ናሉ።”


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለእ​ር​ሱና በቤቱ ላሉት ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።


የም​ኵ​ራብ አለቃ ቀር​ስ​ጶ​ስም ከነ​ቤተ ሰቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አመነ፤ ከቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎ​ችም ብዙ​ዎች ሰም​ተው አም​ነው ተጠ​መቁ።


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”


በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው።


እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።


እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።


ነገር ግን ተስፋ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ይሆን ዘንድ፥ ያመ​ኑ​ትም ያገ​ኙት ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ዘግ​ቶ​ታል።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሆነ​ና​ልና።


跟着我们:

广告


广告