Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 16:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በሰ​ን​በት ቀንም ከከ​ተ​ማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸ​ሎት ቤት ያለ መስ​ሎን ነበ​ርና፤ በዚ​ያም ተቀ​ም​ጠን፥ በዚያ ለተ​ሰ​በ​ሰቡ ሴቶች እና​ስ​ተ​ምር ጀመ​ርን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በሰንበት ቀንም፣ የጸሎት ስፍራ በመፈለግ፣ ከከተማዪቱ በር ወጥተን ወደ አንድ ወንዝ ወረድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በሰንበትም ቀን ለጸሎት ይሰበሰቡበት ወደነበረው ከከተማው ውጪ ወደሚገኘው ወደ ወንዝ ዳር ሄድን፤ እዚያም ተቀምጠን ለተሰበሰቡት ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 16:13
17 交叉引用  

እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።


እንዲህም አላቸው “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።


በሰ​ን​በ​ትም በአ​ንድ ምኵ​ራብ ውስጥ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


እነ​ር​ሱም ከጰ​ር​ጌን አል​ፈው የጲ​ስ​ድያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ በሰ​ን​በት ቀንም ወደ ምኵ​ራብ ገብ​ተው ተቀ​መጡ።


ከም​ኵ​ራ​ብም ከወጡ በኋላ ይህን ነገር በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰን​በት እን​ዲ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸው ማለ​ዱ​አ​ቸው።


ለጸ​ሎት ስን​ሄ​ድም የም​ዋ​ር​ተ​ኛ​ነት መን​ፈስ ያደ​ረ​ባት አን​ዲት ልጅ አገ​ኘ​ችን፤ በጥ​ን​ቈ​ላም የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብዙ እጅ መንሻ ለጌ​ቶ​ችዋ ታገባ ነበር።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤


ጳው​ሎ​ስም እንደ አስ​ለ​መ​ደው ወደ እነ​ርሱ ገብቶ ሦስት ሳም​ንት ከመ​ጻ​ሕ​ፍት እየ​ጠ​ቀሰ ሲከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ሰነ​በተ።


ጳው​ሎ​ስም በየ​ሰ​ን​በቱ በም​ኵ​ራብ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ አይ​ሁ​ድ​ንና አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ያሳ​ም​ና​ቸው ነበር።


ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ።


ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን።


ወዲ​ያ​ው​ኑም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነው” ብሎ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በየ​ም​ኵ​ራ​ቦቹ ሰበከ፥ አስ​ተ​ማ​ረም።


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


እን​ግ​ዲህ ከሰ​ማ​ች​ሁት ከሰ​ማይ በታች በመ​ላው ዓለም ከተ​ሰ​በ​ከው እኔ ጳው​ሎ​ስም አዋጅ ነጋ​ሪና መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ ከተ​ሾ​ም​ሁ​ለት፥ ከወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ተስፋ የመ​ሠ​ረ​ታ​ችሁ አቅ​ዋም ሳይ​ና​ወጥ ጨክ​ና​ችሁ በሃ​ይ​ማ​ኖት ብት​ጸኑ፥


跟着我们:

广告


广告