Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 12:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሄሮ​ድ​ስም በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ሰዎች ተቈ​ጥቶ ነበር፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ወደ እርሱ መጥ​ተው የን​ጉ​ሡን ቢት​ወ​ደድ በላ​ስ​ጦ​ስን እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸው ማለ​ዱት፤ የሀ​ገ​ራ​ቸው ምግብ ከን​ጉሥ ሄር​ድስ ነበ​ርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሱም ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎች ጋራ ጥለኛ ነበር፤ አገራቸው ምግብ የሚያገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበር፣ የንጉሡን ባለሟል የብላስጦስን ድጋፍ ካገኙ በኋላ፣ አንድ ላይ ሆነው ከንጉሡ ጋራ ለመታረቅ ጠየቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፤ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፤ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 12:20
24 交叉引用  

ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል።


እነ​ሆም፥ እን​ጨ​ቱን ለሚ​ቈ​ርጡ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሃያ ሺህ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ የተ​በ​ጠረ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ፥ ሃያ ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ ሃያ ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት በነጻ እሰ​ጣ​ለሁ።”


አሁ​ንም ጌታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ስን​ዴ​ው​ንና ገብ​ሱን ዘይ​ቱ​ንና የወ​ይን ጠጁን ወደ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ይላክ፤


ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።


ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና።


ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ።


ቆጵ​ሮ​ስ​ንም አየ​ናት፤ በስተ ግራ​ች​ንም ትተ​ናት ወደ ሶርያ ሄድን፤ ወደ ጢሮ​ስም ወረ​ድን፤ በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ጭነት ሁሉ በዚያ ያራ​ግፉ ነበ​ርና።


እኛም ከጢ​ሮስ ወጥ​ተን አካ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር መጣን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ን​ንም አግ​ኝ​ተን ሰላም አል​ና​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አንድ ቀን አደ​ርን።


ድን​በ​ሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስ​ፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞ​ራል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ኢያ​ሴፍ ይዞ​ራል፤ መው​ጫ​ውም በሌ​ብና በኮ​ዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤


跟着我们:

广告


广告