Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 12:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሄሮ​ድስ ግን አስ​ፈ​ልጎ ባጣው ጊዜ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን መረ​መረ፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ አዘዘ፤ ከዚ​ህም በኋላ ከይ​ሁዳ ወደ ቂሳ​ርያ ወርዶ በዚያ ተቀ​መጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሄሮድስም ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ፣ ዘብ ጠባቂዎቹን በጥብቅ ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ። ከዚያም ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሄሮድስም አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎችን መረመረ፤ ይገድሉአቸውም ዘንድ አዘዘ፤ ከይሁዳም ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሄሮድስም በበኩሉ ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ዘብ ጠባቂዎችን ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ፤ ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ሄዶ እዚያ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሄሮድስም አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎችን መረመረ ይገድሉአቸውም ዘንድ አዘዘ፤ ከይሁዳም ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 12:19
19 交叉引用  

ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


በነጋ ጊዜም ወታ​ደ​ሮች፥ “ጴጥ​ሮስ ምን ሆነ?” ብለው ታወኩ።


ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።


ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር።


የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም ከእ​ን​ቅ​ልፉ በነቃ ጊዜ በሮች ሁሉ ተከ​ፍ​ተው አየ፤ ሰይ​ፉ​ንም መዝዞ ራሱን ሊገ​ድል ወደደ፤ እስ​ረ​ኞቹ ያመ​ለ​ጡት መስ​ሎት ነበ​ርና።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።


ወታ​ደ​ሮ​ቹም ዋኝ​ተው እን​ዳ​ያ​መ​ልጡ እስ​ረ​ኞ​ችን ለመ​ግ​ደል ተማ​ከሩ።


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።


ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም።


跟着我们:

广告


广告