Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ርዳታውንም በበርናባስና በሳውል እጅ ለሽማግሌዎቹ በመላክ፣ ይህንኑ አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እንዲህም ደግሞ አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ላኩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 መዋጮም አድርገው በበርናባስና በሳውል እጅ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 11:30
21 交叉引用  

በዚ​ያም ወራት ሄሮ​ድስ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ሹሞች ያዛ​ቸው፤ መከ​ራም አጸ​ና​ባ​ቸው።


በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።


እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።


ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስ​ትም ስለ​ዚህ ነገር የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያዩ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።


በየ​ከ​ተ​ማ​ውም ሲሔዱ፥ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያዘ​ዙ​ትን ሥር​ዐት አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው።


ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ።


በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ዘንድ ትር​ጓ​ሜዉ የመ​ጽ​ና​ናት ልጅ የሚ​ሆን በር​ና​ባስ የተ​ባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚ​ሉት አንድ የቆ​ጵ​ሮስ ሰው ነበር።


በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።


በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤


ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።


跟着我们:

广告


广告