Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ስለ​ዚ​ህም ወዲ​ያ​ውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመ​ም​ጣ​ት​ህም መል​ካም አደ​ረ​ግህ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ሁሉ ልን​ሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ አለን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እኔም ወዲያው ላክሁብህ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ እኛ ሁላችን ጌታ ያዘዘህን ስትነግረን ለመስማት በእግዚአብሔር ፊት አለን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ስለዚህ ያንጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ስለዚህ ወዲያውኑ መልእክተኞች ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል፤ እንግዲህ እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት እዚህ ተሰብስበናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ስለዚህ ያን ጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፥ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 10:33
20 交叉引用  

ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።


ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።


የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።


እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው።


ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።


እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አላቸው።


አሁ​ንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባ​ሕር አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት የሚ​ኖ​ረ​ውን ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ፤ እርሱ መጥቶ የም​ት​ድ​ን​በ​ትን ይነ​ግ​ር​ሃል።


ጴጥ​ሮ​ስም አፉን ከፈ​ተና እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት እን​ደ​ማ​ያ​ዳላ በእ​ው​ነት አየሁ።


እን​ግ​ዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገ​ኘች ይህቺ ድኅ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ም​ት​ሆን ዕወቁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ሙ​ታል።”


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


መከራ እቀ​በል በነ​በ​ረ​በት ጊዜ አል​ሰ​ለ​ቻ​ች​ሁ​ኝም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ፥ እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ተቀ​በ​ላ​ች​ሁኝ እንጂ በሰ​ው​ነቴ አል​ና​ቃ​ች​ሁ​ኝም።


ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን ነው? እን​ዳ​ትል ከባ​ሕሩ ማዶ አይ​ደ​ለ​ችም።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።


跟着我们:

广告


广告