Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በቂ​ሳ​ር​ያም ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢጣ​ሊቄ ለሚ​ሉት ጭፍ​ራም የመቶ አለቃ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በቂሳርያ፣ “የኢጣሊያ ክፍለ ጦር” በሚባለው ሰራዊት ውስጥ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በቂሳርያ የሚኖር ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሮማውያን ጦር ሠራዊት ሥር “የኢጣልያ ብርጌድ” በሚባለው ውስጥ የመቶ አለቃ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 10:1
19 交叉引用  

በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ።


አንድ የመቶ አለ​ቃም ነበረ፤ አገ​ል​ጋ​ዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እር​ሱም በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበር።


ጭፍ​ሮ​ችና የሺ አለ​ቃው፥ የአ​ይ​ሁ​ድም ሎሌ​ዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘው አሰ​ሩት።


ይሁ​ዳም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወታ​ደ​ሮ​ችን ተቀ​በለ፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በረ​ዳ​ት​ነት ወሰደ፤ ፋኖ​ስና የችቦ መብ​ራት፥ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዞ ወደ​ዚያ ሄደ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ቂሳ​ርያ ከተማ ገባ፤ ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም ዘመ​ዶ​ቹ​ንና የቅ​ርብ ወዳ​ጆ​ቹን ጠርቶ ይጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር።


ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈል​ገው ብዙ ደበ​ደ​ቡት፤ ወዲ​ያ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ላዋ እንደ ታወ​ከች የሚ​ገ​ልጥ መል​እ​ክት ወደ ሻለ​ቃው ደረ​ሰ​ለት።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።


ሊገ​ር​ፉ​ትም በአ​ጋ​ደ​ሙት ጊዜ ጳው​ሎስ በአ​ጠ​ገቡ የነ​በ​ረ​ውን የመቶ አለቃ፥ “የሮ​ማን ሰው ያለ ፍርድ ልት​ገ​ርፉ ይገ​ባ​ች​ኋ​ልን?” አለው።


ከመቶ አለ​ቆ​ችም ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “ከወ​ታ​ደ​ሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁለት መቶ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ምረጡ፤ ከሌ​ሊ​ቱም በሦ​ስት ሰዓት ወደ ቂሣ​ርያ ይሂዱ” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢ​ውም ደረሱ፤ የተ​ላ​ከ​ው​ንም ደብ​ዳቤ ለአ​ገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም ወደ እርሱ አቀ​ረ​ቡት።


ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።


ጳው​ሎ​ስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለ​ቃ​ውና ለወ​ታ​ደ​ሮቹ፥ “እነ​ዚህ ቀዛ​ፊ​ዎች በመ​ር​ከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አት​ች​ሉም” አላ​ቸው።


የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።


跟着我们:

广告


广告