Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ተሰሎንቄ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዐመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በሐሰት እንዲያምኑ የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የሐሰትን ኑፋቄ በመላክ በስሕተት እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚህ ምክንያት በሐሰት እንዲያምኑ እግዚአብሔር የሚያሳስት ኀይልን ይልክባቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።

参见章节 复制




2 ተሰሎንቄ 2:11
21 交叉引用  

ጌታ​ውም፥ “ባሪ​ያህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገኝ” ብላ የነ​ገ​ረ​ች​ውን የሚ​ስ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።


እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።


እኔ ግን አዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ እፈ​ቅ​ዳ​ለሁ፤ እኔ በጠ​ራሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ በፊ​ቴም ክፉ ነገ​ርን አደ​ረጉ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረጡ።”


ከም​ድ​ራ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ር​ቁ​አ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተም እን​ድ​ት​ጠፉ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና።


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰው​ነ​ታ​ቸው ድረስ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብለህ ይህን ሕዝ​ብና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እጅግ አታ​ለ​ልህ አልሁ።


ነቢ​ዩም ቢታ​ለል፥ ቃል​ንም ቢና​ገር፥ ያን ነቢይ ያታ​ለ​ልሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እጄ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


በተ​ገ​ደ​ሉት ኀጢ​አ​ተ​ኞች አን​ገት ላይ ያኖ​ሩህ ዘንድ ከንቱ ራእ​ይን ሲያ​ዩ​ልህ፥ በሐ​ሰት ምዋ​ር​ትም ሲና​ገ​ሩ​ልህ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀና​ቸው ደረሰ።


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤


ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


ልመናችን ከስሕተት ወይም ከርኵሰት ወይም ከተንኰል አልነበረምና፤


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።


跟着我们:

广告


广告