Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዳዊ​ትም ከላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ መጣ፤ በዚ​ያም መታ​ቸ​ውና፥ “ውኃ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቼን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በፊቴ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም “የላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ” ተብሎ ተጠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህም ዳዊት ወደ በኣልፐራሲም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፣ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፥ ጌታም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። በዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም ባዓል ፈራጺም ተባለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ወርዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል ካደረገ በኋላ “እግዚአብሔር በጠላቶቼ መካከል እንደ ጐርፍ ሰባብሮ ገባ” አለ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “ባዓል ፈራጺም” ተብሎ ተጠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲም መጣ፥ በዚያም መታቸውና፦ ውኃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በፊቴ አፈረሳቸው አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲም ብሎ ጠራው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 5:20
5 交叉引用  

ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


ዳዊ​ትም ወደ በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ወጣ፤ በዚ​ያም ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ​ቸው። ዳዊ​ትም፥ “ውኃ እን​ዲ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቼን በእጄ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ስፍራ ስም በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ብለው ጠሩት።


አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በኃ​ጥ​ኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነ​ሣል፤ በገ​ባ​ዖን ሸለ​ቆም ይኖ​ራል፤ ሥራ​ውን ማለት መራራ ሥራ​ውን በቍጣ ይሠ​ራል፤ ቍጣ​ውም ድን​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ መር​ዙም ልዩ ነው።


ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፣ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፣ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ።


跟着我们:

广告


广告