2 ሳሙኤል 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የዐምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም መፊቦሼት ይባል ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፥ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፥ ፈጥናም ስትሸሽ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበረ። 参见章节 |