2 ሳሙኤል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብንያምም ልጆች የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቈጠራለች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት መኰንኖች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የበኤሮት ተወላጆች የሆኑት የሪሞን ልጆች በዓናና ሬካብ ነበሩ፤ በኤሮት የብንያም ክፍል እንደ ሆነች ይታሰብ ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፥ የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፥ ብኤሮትም ለብንያም ተቆጥራ ነበር። 参见章节 |