Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚያም ዳዊት፥ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እንዲሁም ዳዊት ወደ ኢያቡስቴ መልእክተኞች ልኮ እንዲህ አለው፤ “ሚስቴን ሜልኮልን መልስልኝ፤ እኔ እርስዋን ለማግባት የአንድ መቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ ጥያለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፦ በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ ብሎ መልእክተኞችን ሰደደ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 3:14
7 交叉引用  

የሳ​ኦል ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ዳዊ​ትን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከይ​ሁዳ ወገ​ኖች ብቻ በቀር ሁለት ዓመት ነገሠ።


ኢያ​ቡ​ስ​ቴም ልኮ ከሴ​ሊስ ልጅ ከባ​ልዋ ከፈ​ላ​ጥ​ያል ወሰ​ዳት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው።


የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።


ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው።


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁለት መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ዳዊ​ትም ለን​ጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለ​ባ​ቸ​ውን አም​ጥቶ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ለን​ጉሡ ሰጠ። ሳኦ​ልም ልጁን ሜል​ኮ​ልን ዳረ​ለት።


ሳኦል ግን የዳ​ዊ​ትን ሚስት ልጁን ሜል​ኮ​ልን ሀገሩ ሮማ ለነ​በ​ረው ለያ​ሚስ ልጅ ለፈ​ልጢ ሰጣት።


跟着我们:

广告


广告