Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም፣ “ይሁን ዕሺ፣ ከአንተ ጋራ ስምምነቱን አደርጋለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ አንዲት ነገር እሻለሁ፤ ይኸውም ወደ እኔ ስትመጣ በመጀመሪያ የሳኦልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ እንድትመጣ ነው፤ አለዚያ ግን ወደ እኔ እንዳትመጣ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም፥ “ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም “መልካም ነው! ከአንተ ጋር ስምምነት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንተ በቅድሚያ የምትፈጽምልኝ ነገር አለ፤ ይኸውም ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ይዘህ ካልመጣህ መገናኘት አንችልም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም፦ ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም አለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 3:13
8 交叉引用  

ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል።


አንተ ጌታ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፦ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ላ​መ​ጣ​ች​ሁት ዳግ​መኛ ፊቴን አታ​ዩም አል​ኸን።


እኛም አል​ነው፦ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ካል​ሄደ መሄድ አን​ች​ልም፤ ታናሹ ወን​ድ​ማ​ችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚ​ያን ሰው ፊት ማየት አይ​ቻ​ለ​ን​ምና።


አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ሲዘ​ፍ​ንና ሲጫ​ወት አይታ በል​ብዋ ናቀ​ችው።


跟着我们:

广告


广告