Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 24:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም ቸነ​ፈ​ሩን መረጠ፤ የስ​ን​ዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥ​ዋት እስከ ቀትር ቸነ​ፈ​ርን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ላከ። ቸነ​ፈ​ሩም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጀመረ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚያች ዕለት ጧት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህም ጌታ ከዚያች ዕለት ጥዋት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ ሰው አለቀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚያን ጠዋት ጀምሮ እስከ ወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር አመጣ፤ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ እስራኤላውያን አለቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፥ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ቸነፈሩ በሕዝቡ መካከል ጀመረ፥ ከሕዝቡም ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 24:15
11 交叉引用  

ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን የሠ​ራ​ዊት አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሕ​ዝ​ቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቍጠ​ራ​ቸው” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቸነ​ፈ​ርን ሰደደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።


የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም መቍ​ጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አል​ፈ​ጸ​መም፤ ስለ​ዚህ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በን​ጉሡ በዳ​ዊት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ አል​ተ​ጻ​ፈም።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሚኮ​ሎት አለቃ ነበር፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ቱም የሞ​ቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤


አየሁም፤ እነሆም ሐመር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።


የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።


跟着我们:

广告


广告