2 ሳሙኤል 24:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦስት ዓመት ራብ በሀገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በሀገርህ ላይ ይሁን? የሚሻልህን ምረጥ። አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር” ብሎ ነገረው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፣ “በምድርህ የሦስት ዓመት ራብ ይምጣብህ? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ትሸሽ? ወይስ ደግሞ በምድርህ ላይ የሦስት ቀን መቅሠፍት ይምጣ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ ዐስበህበት ወስን” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፥ “በምድርህ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን፥ ለሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህና በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን የቸነፈር መቅሠፍት ከሚሆን የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስበህበት ወስን” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ጋድ ወዶ እርሱ ቀርቦ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያለውን ነገረው፤ ቀጠል አድርጎም “በምድርህ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን፥ ለሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህና በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን የቸነፈር መቅሠፍት ከሚሆን የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ በብርቱ አስብበትና ወደ እግዚአብሔር የማቀርበውን መልስ ስጠኝ” ሲል ጠየቀው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፦ የሦስት ዓመት ራብ በአገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በአገርህ ላይ ይሁን? አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር ብሎ ነገረው። 参见章节 |