2 ሳሙኤል 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በውኑ ቤቴ በኀያሉ ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በዘመኑ ሁሉ የተዘጋጀና የተጠበቀ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፤ መድኀኒቴም ፈቃዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመፀኛም አይበቅልምና። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 “የእኔስ ቤት በአምላክ ዘንድ ትክክል አይደለምን? ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ ከእኔ ጋራ ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን? ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በሁሉ ነገር ቅንና ጽኑ የሆነውን የዘላለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፥ መድኃኒቴንና ፈቃዴን ሁሉ ያበቅላል። 参见章节 |