Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እር​ሱም ከሦ​ስቱ ይልቅ የከ​በረ ነበር፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አቢሳ ከሦስቱ ይልቅ እጅግ የከበረ አልነበረምን? ከእነርሱ እንደ አንዱ ባይሆንም አለቃቸው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱ ከሠላሳው ይልቅ እጅግ ዝነኛ ስለ ነበር፤ አለቃቸው ሆኖ ነበር፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ ደረጃ አልደረሰም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከሠላሳዎቹ መካከል እጅግ ዝነኛ በመሆኑም የእነርሱ አለቃ ሆነ፤ ይሁን እንጂ የሦስቱን ጀግኖች ያኽል ዝነኛ አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርሱ በሠላሳው መካከል የከበረ አልነበረምን? ስለዚህም አለቃቸው ሆኖ ነበር፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አልደረሰም።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 23:19
9 交叉引用  

ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።


ሦስ​ቱም ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፤ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፈ​ሰ​ሰው።


የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበር። እር​ሱም ጦሩን በሦ​ስቱ መቶ ላይ አን​ሥቶ ገደ​ላ​ቸው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ዘንድ ተጠ​ርቶ ነበር።


በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የዳ​ዊት የአ​ጎቱ ልጅ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን ነበረ፤ ለሰ​ልፍ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በተ​ገ​ዳ​ደሩ ጊዜ ከዳ​ዊት ጋር ከነ​በሩ ከሦ​ስቱ ኀያ​ላን አንዱ እርሱ ነበረ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተመ​ለሱ።


እነሆ፥ ከሠ​ላ​ሳው ይልቅ የከ​በረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም። ዳዊ​ትም በና​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ ሾመው።


በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”


ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።


የፀ​ሐይ ክብሩ ሌላ ነው፤ የጨ​ረ​ቃም ክብሩ ሌላ ነው፤ የከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ክብ​ራ​ቸው ሌላ ነው፤ ኮከብ ከኮ​ከብ በክ​ብር ይበ​ል​ጣ​ልና።


跟着我们:

广告


广告