2 ሳሙኤል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሴሜይ ነበረ። ፍልስጥኤማውያንም በቴሪያ ተሰበሰቡ። በዚያም ምስር የሞላበት የእርሻ ክፍል ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከርሱም ቀጥሎ የሃራራዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ሌሒ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ዕርሻ ላይ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ፣ የእስራኤል ሰራዊት ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከእርሱም ቀጥሎ የሃራርታዊው የአጌ ልጅ ሻማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ምስር በሞላበት ሌሒ በተባለ ስፍራ አንድ እርሻ ላይ በአንድነት ተሰብስበው ነበር። ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከሦስቱ ኀያላን ሦስተኛው ደግሞ የሃራር ተወላጅ የሆነው ዝነኛው የአጌ ልጅ ሻማ ነበር፤ አንድ ቀን ፍልስጥኤማውያን የምስር ማሳ ባለበት በሌሒ ተሰልፈው ነበር፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበረ። ፍልስጥኤማውያንም ምስር በሞላበት እርሻ በአንድነት ሆነው ተካማችተው ነበር፥ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። 参见章节 |