2 ሳሙኤል 21:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያ ጊዜም ኩሳታዊው ሴቦካይ፣ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን፣ ሳፍን ገደለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያን ጊዜም የሑሻው ተወላጅ ሲበካይ፥ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን ሳፍን ገደለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚህ በኋላ ጎብ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደረገ፤ በዚህን ጊዜ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ ሳፍ ተብሎ የሚጠራውን ከራፋይም ወገን የነበረውን ኀያል ሰው ገደለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ፥ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሳፍን ገደለ። 参见章节 |