Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብና የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች ከኬ​ብ​ሮን ወጥ​ተው በገ​ባ​ዖን ውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው፤ በው​ኃ​ውም መቆ​ሚያ በአ​ንዱ ወገን እነ​ዚህ፥ በሌ​ላ​ውም ወገን እነ​ዚያ ሆነው ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኵሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ አንዱ ወገን በኵሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኵሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኲሬ አጠገብ ተገናቿቸው፤ አንዱ ወገን በኲሬው ወዲህ ማዶ፥ ሌላው ወገን ደግሞ በኲሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናቱ ጸሩያ ተብላ የምትጠራው ኢዮአብና ሌሎቹም የዳዊት ባለሥልጣኖች ወጥተው በገባዖን ኲሬ ውሃ አጠገብ ተገናኙ፤ ሁሉም በቡድን ተከፋፍለው በኲሬው ውሃ ማዶ ለማዶ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ባሪያዎች ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፥ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 2:13
13 交叉引用  

በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።


ኢዮ​አ​ብም በእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ አለቃ ነበረ፤


በገ​ባ​ዖ​ንም ወዳ​ለው ወደ ታላቁ ድን​ጋይ በደ​ረሱ ጊዜ አሜ​ሳይ በፊ​ታ​ቸው መጣ፤ ኢዮ​አ​ብም የሰ​ልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላ​ዩም መታ​ጠ​ቂያ ነበረ፤ በወ​ገ​ቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እር​ሱም ሲራ​መድ ሰይፉ ወደቀ።


የዳ​ዊት ኀያ​ላ​ንም ስማ​ቸው ይህ ነው። የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል በሠ​ላ​ሳው መካ​ከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአ​ጎቱ የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፥


የሦ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሒ​ሎ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤


ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።


አን​ተም ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አብ፥ ሁለ​ቱን የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት አለ​ቆች የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን የኢ​ያ​ቴ​ር​ንም ልጅ አሜ​ሳ​ይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ የጦ​ር​ነ​ት​ንም ደም በሰ​ላም አፈ​ሰሰ፤ በወ​ገ​ቡም ባለው ድግና በእ​ግ​ሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።


ዳዊ​ትም ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያ​ንን አስ​ቀ​ድሞ የሚ​መታ ሰው አለ​ቃና መኰ​ንን ይሆ​ናል አለ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ አስ​ቀ​ድሞ ወጣና ወጋ​ቸው፥ አለ​ቃም ሆነ።


እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሶር​ህ​ያና አቢ​ግያ ነበሩ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮ​አብ፥ አሣ​ሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ።


በአ​ራ​ተ​ኛው ወር አራ​ተ​ኛው አለቃ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሳ​ሄል ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ልጁ ዝባ​ድ​ያና ወን​ድ​ሞቹ ነበሩ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


ሠራ​ዊ​ቱ​ንም ሁሉ ይዘው ከና​ታ​ንያ ልጅ ከእ​ስ​ማ​ኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገ​ባ​ዖ​ንም ባለው በብዙ ውኃ አጠ​ገብ አገ​ኙት።


ዳዊ​ትም ኬጤ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንና የሶ​ር​ህ​ያን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ብን ወን​ድም አቢ​ሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚ​ገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ አቢ​ሳም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እገ​ባ​ለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告